የመውጫ ፈተና  ለመውሰድ እየተመዘገባችሁ የምትገኙ አመልካቾች  በሙሉ

የመውጫ ፈተና ለመውሰድ እየተመዘገባችሁ የምትገኙ አመልካቾች ከ OTP ጋር የተያያዘ ችግር ካጋጠማችሁ ወይም OTP ካልደረሳችሁ አቅራቢያችሁ የሚገኝ የፋይዳ አገልግሎት ቢሮ በመሔድ ወይም 9779 ላይ በመደወል ድጋፍ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ስልክ ቁጥርዎን ከቀየሩና OTP በቀድሞ ስልክ ቁጥርዎ ከተላከ፣ አቅራቢያዎ የሚገኝ የፋይዳ አገልግሎት ቢሮ በመሔድ ወይም 9779 ላይ በመደወል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሌሎች መረጃዎች በአግባቡ እስከተሞሉ ድረስ፣ የጾታ እንዲሁም የስልክ ቁጥር አለመመሳሰል ችግር አይሆንም፡፡ ስለዚህ የስልክ ቁጥር እንዲሁም የጾታ አለመመሳሰል ቢኖርም የፋይዳ መታወቂያችሁን በመጠቀም የራስ ማረጋጋጫ (Self-Identity Verification) ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ የተወሰነ የስፔሊንግ ስህተትም ችግር አይሆንም ተብሏል፡፡

ፋይልዎን በ FAN ቁጥርዎ አማካኝነት ማግኘት ካልቻሉ፣ ሁለተኛውን አማራጭ (Bio Data) በመጠቀም ለማግኘት ይሞክሩ፡፡ በሁለቱም አማራጮች ማግኘት ካልቻሉ የትምህርት ተቋምዎን ያነጋግሩ፡፡